1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 10 2016

ለረጅም ዓመታት ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ማእከል የተጓዦችን የፍላጎት እድገት መነሻ ተደርጎ የተሠራ የማዘመን ሥራ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4g1oO
Äthiopien Addis Abeba Ethiopian Airlines Flughafen Ausbau
ምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ 

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጎ እድሳት እና ማስፋፊያ ያደረገበትን የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ዛሬ አስመረቀ።

አየር መንገዱ ካሉት ከ20 በላይ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በቀን በአማካኝ ከ 200 በላይ በረራዎችን እንደሚያደርግ እና በዓመት 3.5 ሚሊዮን መንገደኞችን እንደሚያጓጉዝ ተነግሯል።

አየር መንገዱየሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት ማደጉን ገልጿል። ይህ ሀገሪቱ ካለባት የፀጥታ ሥጋት መነሻ የመንገድ ትራንስፖርትን ከመጠቀም የመቆጠብ አዝማሚያ ስለጨመረ የተከሰተ ሆን ሲል ዶቼ ቬለ ጥያቄ ያቀረበለት አየር መንገዱ "መካከለኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ ቁጥር መጨመር" ያስከተለው ነው ብሏል።

 

ማስፋፊያው የተጓዦችን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ነው

ለረጅም ዓመታት ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ  ማእከል የተጓዦችን የፍላጎት እድገት መነሻ ተደርጎ የተሠራ የማዘመን ሥራ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቻይና የግንባታ ሥራ ድርጅት የተገነባው ይህ የእድሳት እና የማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሊኖር የሚችለውን የሀገር ውስጥ መንገደኞች ፍላጎት ታሳቢ ተደርጎ መሠራቱንም ገልፀዋል።

"ይህ ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በዓመት የሚያስተናግዳቸው መንገደኞች በእጥፍ እንዲያድግ ታሳቢ ተደርጎ የማስፋፊያ እና የእድሳት ሥራ የተደረገበት ነው"

[የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ 

ዳግም የተጀመሩ በረራዎች 

ተቋርጦ የነበረው የደንቢ ዶሎ በረራ ጀምሯል ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በቅርቡ ወደ ነቀምት ከተማ አዲስ በረራ እንደሚጀመር እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ለዓመታት ሥራ አቆሞ ወደቆየው አክሱም በቅርቡ በቀን አንድ በረራ ይጀመራል ብለዋል። አየር መንገዱ በውስጡ ለሚፈፀሙ ብልሹ አሠራሮች "ምንም ቦታ እንደማይሰጥ" እና እርምጃዎችን መውሰዱን እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት የጨመረው በምን ምክንያት ነው? 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ ምስል Solomon Muche/DW

በቀን በአማካኝ ከ 200 በላይ በረራዎችን በማድረግ አገልግሎት ይሰጣል የተባለውየኢትዮጵያ አየር መንገድበዓመት 3.5 ሚሊዮን መንገደኛ ይህንን የአየር መንገዱን አገልግሎት እየተጠቀሙ ስለመሆኑም ተገልጿል። ይሁንና የሀገር ውስጥ የበረራ ፍላጎቱ መጨመር ሀገሪቱ ከገጠማት የፀጥታ ችግር መነሻ የየብስ ትራንፖርት በተጋረጠበት ፈተና አውሮፕላን ምርጫ ውስጥ በመግባቱ ስለመሆኑ ይነገራል። ይህንኑ በተመለከተ የጠየቅናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያደቻ ጉዳዩ በተቃራኒው ነው ይላሉ። እንዴት ? 

"መካከለኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ነው ያለው። የዚያ መጨመር የአገልግሎቱን ፍላጎት ያመጣ ነው ብየ አስባለሁ።"

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገው የሀገር ውስጥ ተጓዦች የማስፋፊያ ተርሚናል ግንባታ ለ22 ቱ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹ መንገደኞች የተሻለ ጥራት ያለው ግልጋሎት ለመስጠት ያስችላል፣ የጎብኝዎችንም እንቅስቃሴ ይደግፋል ተብሏል።

ሰሎሞን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር