ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ መዳከሙ የብዙዎች መነጋገሪያ ከሆነ ሰነባበተ። በምክንያትነት አብዛኞቹ የገዢውን ፓርቲ የተጠናከረ ጫና በዋናነት ሲገልጹ፤ የራሳቸው የፓርቲዎቹ እራስን እየተቹና እያረሙ የማደግ ድክመትም ለውጪው ጫና ተጋላጭ እንዳደረጋቸው የሚያነሱም አሉ። በዚያም ላይ የኅብረተሰቡ ከምን በላይ የምሁራን የፖለቲካ ተሳትፎ ውስን መሆን በሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመዳከማቸው መንስኤ እንደሆነም ያስረዳሉ።